በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት፣ ከአፍሪካ ኅብረት ምክትል ሊቀ-መንበር ሀዳዲን ጋር ተወያይተዋል።
መሪዎቹ በውይይት መድረካቸው ወቅት ኢትዮጵያ ለነገው ጠቅላላ ምርጫ ያደረገችውን የዝግጅት ሁኔታ የተመለከቱ ጉዳዮችን አንስተው መክረዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በአህጉሪቱ የእርቀ-ሰላምና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደትን ይበልጥ ለማጠናከር የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች ያላቸውን ተፅዕኖ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።