በኢራን እና በአሜሪካ እስራኤል መካከል የቀጠለውን ጦርነት ተከትሎ ተዘግቶ የቆየው ስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ ወሽመጥ፣ ዳግም ሊከፈት የሚችልበትን መንገድ የኢራን ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
እንደ ጽሕፈት ቤቱ መግለጫ ከሆነ፣ ወሽመጡ ክፍት ሆኖ የንግድ መርከቦች እንዲንቀሳቀሱ የሚፈቀደው ከወሽመጡ የሚገኘው የትራንዚት ገቢ ኢራንን ሲክስ ነው::
ይህም ማለት ገቢው ኢራን በጦርነቱ ምክንያት የደረሰባትን ውድመት መተካት በሚችልበት ደረጃ ላይ ሲደረስ ብቻ ይሆናል።
ይህ ውሳኔ ይፋ የተደረገው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በኢራን እና በኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታዎች እንዲሁም በባለሙያዎች መካከል የተደረገውን ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ተከትሎ መሆኑን ቲአርቲ ዎርልድ በዘገባው አስነብቧል።
በውይይቱ ላይ ይህ ወሳኝ የባሕር መስመር ለዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆንና ዳግም ወደ ሥራ እንዲመለስ ስለሚቻልባቸው አማራጮች ሰፊ ምክክር ተደርጓል።
ምንም እንኳን ወሽመጡን ለመክፈት የካሳ ክፍያ እንደ ቅድመ ሁኔታ ቢቀመጥም፣ የዲፕሎማሲያዊ ጥረቶቹ መቀጠል ለዓለም አቀፍ የንግድ ፍሰት መረጋጋት እንደ መልካም ጅምር ተወስዷል።
#EthiopianBroadcastingCorporation #Iran #HormuzStrait #GlobalTrade #Diplomacy #MaritimeSafety