Search

ፓኪስታን በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የሚደረግ ሁለተኛ ዙር ድርድርን ለማስተናገድ ሐሳብ አቀረበች

ማክሰኞ ሚያዝያ 06, 2018 89

ፓኪስታን የ15 ቀኑ የተኩስ አቁም ስምምነት ከማብቃቱ በፊት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረግ ሁለተኛ ዙር ድርድር በኢስላማባድ ለማስተናገድ ሐሳብ ማቅረቧን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።
የዜና ወኪሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሁለት የፓኪስታን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሀገሪቱ ይህንን ጥያቄ ያቀረበችው ውጥረቱን በዘላቂነት ለመቀነስ ካላት ፍላጎት በመነሣት ነው።
የሐሳቡ ተግባራዊነት የሚወሰነው ተደራዳሪ ወገኖቹ ሌላ የተለየ ቦታ እንዲመቻችላቸው የሚጠይቁ መሆን አለመሆኑ ላይ እንደሆነ ባለሥልጣናቱ መግለጻቸው ተጠቁሟል።
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ሁለተኛው ዙር ድርድር በቅርብ ቀናት ውስጥ፣ ምናልባትም ሐሙስ ዕለት ሊደረግ እንደሚችል ተዘግቧል።