Search

አይ ኤምኤፍ የ2026 የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያውን ይፋ አደረገ፤ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ዕድገት ቀዳሚነቱን ይዛለች

ሓሙስ ሚያዝያ 08, 2018 97

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በአውሮፓውያኑ 2026 የሰሃራ በታች አፍሪካ ሀገራትን የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያ ይፋ አድርጓል።

በዚህ ትንበያ መሠረት ኢትዮጵያ በ9.2 በመቶ ከፍተኛ ዕድገት በማስመዝገብ ከቀጣናው ሀገራት ቀዳሚነቱን እንደምትይዝ ተመልክቷል።

እንደ አይኤምኤፍ ሪፖርት፣ ኡጋንዳ በ7.5 በመቶ፣ ሩዋንዳ በ7.2 በመቶ እንዲሁም ቤኒን በ7.0 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግቡ ተተንብዮላቸዋል።

በሌላ በኩል እንደ ናይጄሪያ (4.1 በመቶ) እና ደቡብ አፍሪካ (1.0 በመቶ) ያሉ የክፍለ አህጉሩ ግዙፍ ኢኮኖሚዎች ዝቅተኛ የዕድገት ትንበያ ተቀምጦላቸዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ግጭት የነዳጅ እና የማዳበሪያ ዋጋን በመጨመር በበርካታ ሀገራት ላይ የኢኮኖሚ ጫና ቢፈጥርም፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት ግን አሁንም ጠንካራ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንደሚያሳዩ የአይኤምኤፍ ትንበያ ያመላክታል።

#IMF #EconomicProjections #Africa #Ethiopia #GDPGrowth #EBC