በሊባኖስ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁሉም የንግድ መርከቦች ክፍት መሆኑን የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ባለበት ጊዜ ሁሉ ማንኛውም የንግድ መርከብ ያለምንም እንቅፋት በወሽመጡ ማለፍ ይችላል።
ኢራን ጊዜያዊ የተኩስ አቁምን እንደማትቀበልና ይልቁንም በመላው ቀጣናው ለተቀሰቀሰው ጦርነት ዘላቂ መፍትሔ እንዲመጣ እንደምትፈልግ የሀገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጸዋል።
ይህ ውሳኔ በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ያለውን ውጥረት ያረግባል ተብሎ ይጠበቃል።