Search

በ2ኛ ዙር ድርድር ለመሳተፍም ሆነ ልዑክ ወደ ፓኪስታን ለመላክ ያሳለፍኩት ውሳኔ የለም - ኢራን

እሑድ ሚያዝያ 11, 2018 72

በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው ውጥረት አገርሽቷል።

የኢራን መንግሥታዊ የዜና ወኪል (IRNA) እንደዘገበው፣ ኢራን “ከአሜሪካ ጋር ለሁለተኛ ዙር ድርድር ለመቀመጥ ያደረግኩት ምንም ዓይነት ስምምነት የለም” ስትል ማስተባበያ ሰጥታለች።

የኢራኑ ተስኒም (Tasnim) የዜና ወኪል እንደዘገበው፣ ኢራን የድርድር ልዑክ ወደ ፓኪስታን ለመላክ ያሳለፈችው ምንም ዓይነት ውሳኔ የለም።

የኢራን ተደራዳሪ ቡድን በግልጽ እንዳሳወቀው፦ አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው "የባሕር ላይ እገዳ" እስካልተነሳ ድረስ ኢራን ወደ ድርድር ጠረጴዛ አትመጣም፤ ምንም ዓይነት ንግግርም አይኖርም።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በድርድሩ የሚሳተፍ የአሜሪካ ልዑክ ወደ ፓኪስታን እየላኩ መሆኑን እና ቡድኑም ሰኞ ምሽት እዚያ እንደሚደርስ ገልጸው ነበር።

ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች ያሉት ትራምፕ፣ "ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ የድርድር ሀሳብ አቅርበናል፤ በውድም ይሁን በግድ ስምምነቱ ይከናወናል” ሲሉ ገልጸዋል።

ኢራን የድርድር ሀሳቡን እንደምትቀበለው ተስፋ አደርጋለሁ ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ይህ ካልሆነ ግን ሀገራቸው ወደማያዳግም የኃይል እርምጃ እንደምትገባ ዝተዋል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

#MiddleEast #Iran #US #Islamabad #talks #negotiation