Search

"ኢራን ያቀረበችው አዲስ የሰላም ዕቅድ አላረካኝም፦ ፕሬዚዳንት ትራምፕ

ዓርብ ሚያዝያ 23, 2018 75

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሁለት ወሩን የአሜሪካ-ኢራን ጦርነት ለማስቆም ከቴህራን የቀረበውን አዲስ የሰላም ሀሳብ ብዙም አላረካኝም በማለት ገልጸውታል።
ትራምፕ በዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ፣ ኢራን ስምምነት ለማድረግ ብትፈልግም ያቀረበችው ሀሳብ ግን ተቀባይነት የሌላቸው ነጥቦች እንዳሉበት ገልጸዋል።
"ኢራን ስምምነት ትፈልጋለች፤ ምክንያቱም ወታደራዊ አቅሟ ተሟጥጧል" ያሉት ትራምፕ፣ በቀረበው ሰነድ ግን እንዳልረኩ እና ኢራን መስማማት የምትችልበት ደረጃ ላይ መሆኗን እንደሚጠራጠሩ ተናግረዋል።
በኢራን ከፍተኛ አመራሮች መካከል "ከባድ አለመግባባት" እንዳለ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ ይህም የሰላም ሂደቱን አስቸጋሪ እንዳደረገው ጠቁመዋል።
ፓኪስታን በሽምግልናዋ የቀጠለች ሲሆን፣ አዲሱን የኢራን የሰላም ሀሳብ ለአሜሪካ ያቀረቡት የፓኪስታን ባለስልጣናት ናቸው።
ትራምፕ ለፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሸሪፍ እና ለሀገሪቱ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት ያላቸው አማራጭ "ወይ ስምምነት ማድረግ ወይም ኢራንን በከባድ ወታደራዊ እርምጃ ማጥፋት" እንደሆነ ፕሬዚዳንት ትራም በግልጽ ተናግረዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) ወታደራዊ አማራጮችን አጥንቶ እንዳቀረበላቸው የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ ከሰብዓዊነት አንጻር ግን በቦምብ የመደብደብ እርምጃን እንደማይመርጡ ጠቁመዋል።
በነስሩ ጀማል