Search

ከሀገር ውስጥ ተቋማዊ ግንባታ እስከ ቀይ ባሕር ሕጋዊ መብት፤ አሰባሳቢው ሀገራዊ ትርክት

ረቡዕ ግንቦት 12, 2018 155

ኢትዮጵያ በታሪኳ የብዙ ማንነቶችና የግዙፍ ታሪኮች ማህደር ብትሆንም፣ 2010 በፊት በነበሩት ሁለት አስርት ዓመታት በፖለቲካው ምህዳር የነገሱት ትርክቶች እንደ አስተሳሳሪ ሳይሆን በሁለት ጎራ ተከፍለው ሀገራችንን ሲያዳክሙ ቆይተዋል።

ይህ በሁለት ጽንፎች መካከል የነበረ የጥላቻ ፖለቲካና የነጣጣይ ትርክቶች አዙሪት አሁን በአዲሱየመደመርእሳቤ የተሰበረ ሲሆን፣ አዲሱ እሳቤ እነዚህን የቆዩ ስብራቶች በመጠገን ሀገራዊ ብርብሔራዊ አንድነትንና የጋራ ተስፋን ሰንቆ ብቅ ብሏል።

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ፍቃድ ተሰማ እና የታሪክ ምሁሩ አየለ በከሪ (/) ለኢቲቪ "አዲስ ቀን" በሰጡት ማብራሪያ፣ ይህ አዲስ ትርክት ኢትዮጵያን ከአዙሪት አውጥቶ ወደ ታላቅነት እንዴት እየመራት እንደሚገኝ በሰፊው አብራርተዋል።

አቶ ፍቃድ ተሰማ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ለዓመታት በሦስት ዋና ዋና ስብራቶች ውስጥ ማለትም በፖለቲካ፣ በዴሞክራሲ ተቋማት እና በተቋማት ግንባታ ስብራት አዙሪት ውስጥ ስትማቅቅ ቆይታለች።

እነዚህም እኔ ካላሸነፍኩ ሀገር ትፍረስ የሚል ጽንፈኝነት፣ ሀገራችንን የሚመስሉ ጠንካራ ተቋማት አለመኖር እንዲሁም አንድ ፓርቲ ሲመጣ አፍርሶ ሌላ የሚገነባበት የተቆራረጠ ጉዞ እንደ ሀገር ትልቅ ዋጋ ሲያስከፍሉን መቆየታቸውን ነው የታነገሩት

መደመር ያለፈውን ታሪክ በጭፍን እንደማይቀበልና በጭፍንም እንደማይቃወም የገለጹት ሚኒስትሩ፣ መልካሙን ወርሰን ግድፈቶቹን ደግሞ ተምረንባቸው የምናልፍበት ድልድይ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ይህ የመደመር እሳቤ ከሀገር ውስጥ ፖለቲካ አልፎ የኢትዮጵያን ስልታዊ ጥቅሞች ማስከበር ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የታሪካዊ ጠላቶች ሴራ መነሻውም ኢትዮጵያ በሁለቱ የውኃ አካላት ማለትም በዓባይ በቀይ ባሕር ላይ ያላትን መብት ለማዳከም መሆኑን ጠቁመዋል።

ዳሴ ግድብ በገንዘብና በባለሙያ ብቻ ሳይሆን በጸጥታ ኃይሎቻችን መስዋዕትነት የተገነባ የድላችን አምድ እንደሆነና የቀይ ባሕርን ጋዊ መብት መጠየቅም የሉዓላዊነትና የህልውና ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል የታሪክ ምሁሩ አየለ በከሪ (/) የኢትዮጵያ ትርክት ገር በቀል ብቻ ሳይሆን አህጉራዊ ፋይዳውም የላቀ መሆኑን ገልጸው፣ ኢትዮጵያ የዓድዋ ድል ባለቤት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መናገሻ የሆነችው በአጋጣሚ ሳይሆን በከፈተችው የነጻነት መንገድ መሆኑን አስታውሰዋል።

/ አየለ አሁንም ድረስ ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚሰሩ የውክልና (Proxy) ጦርነቶችን ነቅቶ መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበው፣ ታሪካችንን የምንሞግተው ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ጭምር መሆኑንና ኢትዮጵያ በአዲሱ ትርክት ግጭትን ወደ ስምምነት፣ ልዩነትን ደግሞ ወደ ውበት እየቀየረች መሆኑን አስረድተዋል።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ የቆመችው በጥላቻ ምሽግ ሳይሆን በትላንት፣ ዛሬና ነገን በሚያስተሳስር አሰባሳቢ ትርክት ላይ ሲሆን፣ መደመር የፖለቲካ ቁማርን ሰብሮ፣ ተቋማዊ ብቃትን ገንብቶና የውጭ ሴራዎችን አክሽፎ ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና ማማ የማውጣት ታሪካዊ ተልዕኮውን እያሳካ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ጭምር ትልቅ ምሳሌ የሚሆን ነው።

በላሉ ኢታላ