Search

በአዲስ አበባ የተካሄደው የዒድ አል አድሃ (ዓረፋ) በዓል ሶላት ሥነ-ሥርዓት በስኬት ተጠናቀቀ

ረቡዕ ግንቦት 19, 2018 135

በመዲናችን የዒድ አል አድሃ (ዓረፋ) በዓል ሶላት ሥነ-ሥርዓት በስኬት መጠናቀቁን እና ለተሽከርካሪ ዝግ የነበሩ መንገዶች መከፈታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የሶላት ሥነ-ሥርዓት የሃይማኖት አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮች፣ የውጭ ሀገር ዜጎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የሶላት ሥነ-ሥርዓቱ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም ተብሎ ለተሽከርካሪ ዝግ የነበሩ መንገዶቸ መከፈታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

ለፕሮግራሙ ስኬታማነት አስተዋፆኦ ላደረጉ አካላት፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች እና አባላት ዋና ጠቅላይ መምሪያው ምስጋናውን አቅርቧል።

ለመላው የእምነቱ ተከታዮችም በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።