Search

መንግሥት ሁሉንም በፍትሃዊነት የጋራ ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሥራ እየሠራ ነው- ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

ረቡዕ ግንቦት 19, 2018 61

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ምርቃት ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንደገለጹት የለውጡ መንግሥት ከኢኮኖሚ እና ከፖለቲካ ተሳትፎ ርቀው የነበሩትን የማኅበረሰብ ከፍሎች ወደ ማዕከል በማምጣት እውነተኛ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) የሚመራው መንግሥት ርቆ የነበረውን በማቅረብ የተገለሉ የሀገራችን ክፍሎችን በፍትሃዊነት የጋራ ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሥራ እየሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም እንደ ሀገር እና እንደ ክልል በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በተቀመጡ ግልፅ የልማት አቅጣጫዎች መሰረት ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በዚህም ህዝቡ በግብርና፣ በማዕድን፣ በኢንዱስትሪ እና በቱሪዝም ዘርፎች ያለውን ፀጋ አሟጥጦ በመጠቀም ከሴፍቲኔት ጥገኝነት በመላቀቅ በራሱ ላብ እና ጥረት ሕይወቱን እንዲቀይር ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን አስታውቀዋል፡፡

አዲሱ ትውልድም በዲጂታሉ ዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆን በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በተለይም አዲሱ ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ በየብስ ጉዞ አስር ሰዓት ይወስድ የነበረውን ርቀት ወደ አንድ ሰዓት በማሳጠር የቦረናን ሕዝብ ከማዕከል ጋር በቅርበት እንዳገናኘው አቶ ሽመልስ ገልጸዋል፡፡

ይህ ግዙፍ መሰረተ ልማት የቦረናን ሕዝብ የእንስሳት ሀብት በቀላሉ ከገበያ ጋር በማስተሳሰር የኑሮ ለውጥ እንዲያመጣ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰው፣ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡

በለሚ ታደሰ