Search

"በምሥራቅ ቦረና ዞን እየታየ ያለው የግብርና ትራንስፎርሜሽን፤ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል ለምታደርገው ጉዞ ትልቅ ማረጋገጫ ነው!" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ረቡዕ ግንቦት 19, 2018 73

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "በምሥራቅ ቦረና ዞን እየታየ ያለው የግብርና ትራንስፎርሜሽን፤ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል ለምታደርገው ጉዞ ትልቅ ማረጋገጫ ነው" ሲሉ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “በዚህ ወቅት ብቻ ታታሪ አርሶ አደሮቻችን ከ176 ሺህ 223 ሄክታር በላይ መሬት በማልማት፣ ከ3.1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚያገኙ ይጠበቃል” ብለዋል።

ከ101 ሺህ በላይ አባወራዎችን እና እማወራዎችን በማሳተፍ እና ዘመናዊ ትራክተሮችን በመጠቀም፣ በተደራጀ የክላስተር እርሻ አማካኝነት እምቅ አቅማችንን ወደ ምርታማነት እየቀየርን እንገኛለን ሲሉም አክለዋል።

በምሥራቅ ቦረና ዞን ሊበን ወረዳ ከሚገኙት ሰፋፊ የስንዴ ክላስተሮች ጀምሮ እስከ ዋና ዋናዎቹ የጤፍ፣ የበቆሎ እና የቦሎቄ ምርቶች ድረስ የሚታዬው ውጤት፤ የሀገር ውስጥ የምግብ አቅርቦታችንን የማረጋገጥ ጉዞ ላይ ለመገኘታችን ሕያው ምስክር እንደሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለጹት።