የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን ቀጣናዊ ትብብር፣ የአቅም ግንባታ እና ስትራቴጂካዊ ውይይት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሥልጠና ለደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶች መስጠት ጀምሯል።
የሥልጠና መርሐ ግብሩን በይፋ የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ትሥሥር አውስተዋል።
ይበልጥ ጠንካራ የሆነ የጋራ መጻኢ ዕድልን ለመቅረጽም የታማኝነት፣ የትብብር እና የዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ወሳኝ መሆናቸውን በድጋሚ አረጋግጠዋል።
በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ቶክ ዴንግ፣ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ላዘጋጀው ለዚህ ጠቃሚ የሥልጠና ፕሮግራም ለመጡት የሀገራቸው ዲፕሎማቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አምባሳደሩ በንግግራቸው፤ የአቅም ግንባታን፣ ንቁ ተሳትፎ የሚታይበትን የልምድ ልውውጥ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን የቅንጅት ሥራ ይበልጥ እያሳደገ የመጣውን ጥልቅ ታሪካዊ ትሥሥር አጉልተው አሳይተዋል።
በሕይወት አበበ