Search

ለነገዋ ኢትዮጵያ የተጣለ አረንጓዴ መሠረት - ኢትዮጵያን ያለበሰው የ8 ዓመታት አኩሪ ጉዞ

ቅዳሜ ግንቦት 29, 2018 7

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀሳብ አመንጪነት እና አስተባባሪነት ኢትዮያን ከበረሃማነት በመታደግ አረንጓዴ ገጽታዋን የመመለስ ትልቅ ራዕይ ሰንቆ የተጀመረ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው።

በአረንጓዴ አሻራ 2011 እስከ 2018 . ባለፉት 8 ዓመታት ኢትዮያውያንን ከዳር እስከዳር በማስተባበር አስደናቂ የስኬት ታሪክ ተጽፏል።

የመርሀ ግብሩ ጅማሮ 2011 . ሲከፈት 4 ቢሊዮን በላይ ችግኞች በመትከል የነገዋን አረንጓዴ ኢትዮጵያ መሰረት ጥሏል። 2012 . "በመትከል ማንሰራራት" በሚል አገራዊ ስሜት 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል።

በአረንጓዴ አሻራ ላይ የህዝቡ ተነሳሽነት ይበልጥ እያደገ መጥቶ 2013 . ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናልብስ በሚል መሪ ቃል 6.8 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መሬት የነኩ ሲሆን፣ 2014 . ደግሞ አሻራችንን ለልጆቻችን በሚል ራዕይ 7.2 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል።

የአረንጓዴ አሻራ ባህል በሕዝቡ ዘንድ ጠንካራ መሠረት እየያዘ መጥቶ 2015 . አሻራችን ለትውልዳችን፤ ለትውልድ እንስራ፤ ለኢትዮጵያ እንትከል በሚል መሪ ሀሳብ 7.5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል።

2016 . ደግሞ ''የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ'' በሚል መሪ ቃል በተመሳሳይ 7.5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የኢትዮያን ምድር አልብሰዋል።

ኢትዮያውያን አምና 2017 . ይህ ቁጥር የአገራችንን አልፎ ዓለም አቀፍ ክብረወሰን ጭምር ሰብሮ 8 ቢሊዮን በላይ ችግኞች በመትከል ማሳካት ተችሏል።

የዘንድሮው 2018 . መርሀ ግብርም ይህንኑ የዕድገት ጉዞ በማስቀጠል 8 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ይተከላሉ ተብሎ ታቅዷል። 

ይህ የስምንት ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ ጉዞ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ትግል ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየ አኩሪ አገራዊ ድል ነው።