የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሚገኙ እና በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የአጀንዳ ሃሳቦችን ማሰባሰቡ የሚታወቅ ነው።
በዚህ የምክክር ሂደት በክልል/ ከተማ አስተዳደር ደረጃ፣ በፌዴራል ደረጃ እንዲሁም በዲያስፖራው ማህበረሰብ ዘንድ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች በኮሚሽኑ ተደራጅተው ለመጨረሻው የአጀንዳ ቀረፃ እየተዘጋጁ ነው።
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ ተሳትፎን የሚያደርጉ አካላት ኮሚሽኑ አጀንዳ ካሰባሰበባቸው ባለድርሻ አካላት የተመረጡ/ የተወከሉ ሲሆን ይህም በባለድርሻ አካላቱ እውቅና ሲከናወን ቆይቷል፡፡
በዚህ መሰረት በክልሎች/ ከተማ አስተዳደሮች፣ እና በዲያስፖራው ማህበረሰብ ዘንድ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በአጀንዳ ማሰባሰብ ወቅት በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው ላይ እነሱን ወክለው የሚመካከሩ ወኪሎቻቸውን እንዲመርጡ ተደርጓል።
በሌላ በኩል በኩሚሽኑ አሰራር ስርዓት መሰረት በክልሎች/ከተማ አስተዳደሮች እና በፌዴራል ተቋማት በሚገኙና ወኪሎቻቸውን በአጀንዳ ማሰባሰብ ወቅት እንዲመርጡ ያልተደረጉ ባለድርሻ አካላት ወኪሎቻቸውን በደብዳቤ ወክለው ለኮሚሽኑ እንዲያሳውቁ ኮሚሽኑ ለባለድርሻ አካላቱ ጥሪ በማስተላለፍ ላይ ይገኛል።
በዚህ መሰረት በአጠቃላይ 4,000 የሚጠጉ ተሳታፊዎች የሚሳተፉበት የሀገራዊ ምክክር ሂደት
የየወረዳው የሕብረተሰብ ክፍል ወኪሎችን
የክልል/ከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ወኪሎችን
የፌዴራል ባለድርሻ አካላት ወኪሎችን እና
የዲያስፖራ ማህበረሰብ ወኪሎችን ያሳትፋል፡፡