Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በመጠቀም የተገነቡ ቤቶችን የሚያሳይ የግንባታ ሳይት ጎበኙ

ማክሰኞ ሰኔ 02, 2018 117

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባቸውን ተከትሎ፣ እጅግ ዘመናዊ እና ፈጣን የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በመጠቀም የተገነቡ ቤቶችን የሚያሳይ የግንባታ ሳይት መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ በዚህ ሳይት ሦስት የላቁ የግንባታ ዘዴዎች በጥምረት ጥቅም ላይ ውለዋል፤ 3 ሕትመት (3D printing) የቅድመ-ዝግጅት ቀላል የአረብ ብረት ግንባታ እና የኮንቴይነር መኖሪያ ቤቶች ናቸው ብለዋል።

እያንዳንዳቸው ግንባታዎች ትክክለኛውን ቴክኖሎጂ ስንጠቀም ፍጥነት እና ጥራት እርስ በእርስ የማይጋጩ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፤ ጥራታቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን ከወራት እና ከዓመታት ይልቅ በጥቂት ቀናት እና ሳምንታት ውስጥ ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል የታየበት ሕያው ምስክር መሆናቸውን ነው የጠቆሙት።

ይህ ዓይነቱ የላቀ ፈጠራ በየትኛውም የሀገራችን ክፍል በቀላሉ ሊተገበር፣ ሊደገም እና ሊስፋፋ የሚችል በመሆኑ የሀገራችንን የቤት ልማት ፕሮግራም አቅጣጫ በከፍተኛ ደረጃ የመቀየር ኃይል አለው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

ቴክኖሎጂን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር አጣምረናል፤ መሰል በተግባር የተገለጡ ሥስራዎቻችን ደግሞ ለሀገር የሚገባውን ፈጣን ዕድገት እውን ለማድረግ በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ በቁርጠኝነት እየተጓዝን መሆናችንን በተግባር አሳይቷል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።