Search

በተደራሽነትም ሆነ በተገልጋይ እርካታ ከፍተኛ ስኬት እያስመዘገቡ የሚገኙት የአዲስ መሶብ ማዕከላት

ረቡዕ ሰኔ 03, 2018 64

 

"አዲስ መሶብ" አንድ ማዕከላት ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት፡ ስራ ከጀመሩበት አጭር ጊዜ ጀምሮ 230 ሺህ በላይ ህዝብን በማስተናገድ 99 በመቶ የተገልጋዮች እርካታን አስመዝግበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እና ለአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የተወጠነው "አዲስ መሶብ" ፕሮጀክት ታላቅ ስኬት እያስመዘገበ ይገኛል።

እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 . ድረስ 11 ማዕከላትን ለመክፈት ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን፣ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2018 . ድረስ 9 ማለትም አራዳ፣ ቦሌ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ አዲስ ከተማ፣ ጉለሌ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ እና የካ ሙሉ በሙሉ ወደ አገልግሎት ማስገባት ተችሏል።

የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ደሳለኝ ተረፈ (/) እንደገለጹት፣ ቀሪዎቹ የአቃቂ እና የለሚ ኩራ ማዕከላት የግንባታ አፈጻጸማቸው 99.5 በመቶ በላይ በመሆኑ በቀጣይ ቀናት ተመርቀው አገልግሎት መጀመር የሚያስችላቸው ዝግጅት ተጠናቋል።

ማዕከላቱ ስራ ከጀመሩበት አጭር ጊዜ ጀምሮ 230 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ያስተናገዱ ሲሆን፣ በተደረገው ዳሰሳም የተገልጋዮች እርካታ 99 በመቶ መድረስ መቻሉን መግለጻቸውን የከተማዋ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ይህ ስኬት ሊመዘገብ የቻለው በከተማ አስተዳደሩ ልዩ ድጋፍ የባለሙያ ቅጥር፣ ስልጠና እና መሰረታዊ ግብዓቶች ቀድመው በመሟላታቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል።