Search

የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከቦች የአሜሪካን እገዳ አለፉ

ረቡዕ ሰኔ 10, 2018 101

 

ዋሽንግተን እና ቴህራን ጦርነታቸውን ለማቆም የሚያስችል ማዕቀፋዊ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ፣ በርካታ የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የተጣለውን የአሜሪካ የባሕር እገዳ መስመር ጥሰው ማለፋቸው ተሰምቷል።

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ተጨማሪ ውይይቶችን ለማድረግ እና የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም ሁለት ቀናት ሲቀራቸው፣ የመርከቦችን እንቅስቃሴ የሚከታተለውታንከር ትራከርስየተባለው ድረ-ገጽ የኢራን መርከቦች እገዳውን ማለፋቸውን ይፋ አድርጓል።

ድረ-ገጹ በዲጂታል መከታተያ መረጃዎች እና በሳተላይት ምስሎች ላይ በመደገፍ፣ ኢራን ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳጅ ምርት ወደ ውጭ መላክ መጀመሯን ዛሬ አስታውቋል።

በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት የካቲት 28 ቀን የተቀሰቀሰውን ጦርነት በዘላቂነት ለማቆም የሚደረገው የመጨረሻው የሰላም ንግግር፣ የፊታችን ዐርብ በስዊዘርላንድ ቡርገንስቶክ ተራራማ የመዝናኛ ስፍራ እንደሚጀመር ይጠበቃል።

የሆርሙዝ ወሽመጥ ዳግም ይከፈታል የሚለው ዜናም በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ቅናሽ እንዲታይ አድርጓል።

ታንከር ትራከርስ እንዳመለከተው፣ዲዮናእናሄሮ 2” የተሰኙ የኢራን ብሔራዊ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ኩባንያ መርከቦች በድምሩ 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ በመጫን ማክሰኞ ዕለት የእገዳ ቀጣናውን አልፈዋል።

በተመሳሳይስትሪምየተሰኘችው ሌላኛዋ መርከብ ረቡዕ ዕለት ወደ ኢራን ወደቦች እያመራች የነበረች ሲሆን፣ በዚሁ ዕለት 1 ሚሊዮን በርሜል የኢራን ድፍድፍ ነዳጅ የጫነች ሦስተኛዋ የኩባንያው መርከብ በኦማን ባሕረ ሰላጤ ላይ የተጣለውን የአሜሪካ ባሕር ኃይል እገዳ አልፋ መጓዟን አልጄዚራ ዘግቧል።