Search

"ሰላማዊና ተዓማኒ ምርጫ በማካሄድ ኢትዮጵያውያን በፅናት አዲስ ታሪክ ጽፈዋል"፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ረቡዕ ሰኔ 03, 2018 51

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ በምርጫ ሥራዎቻችን አፈጻፀምና የድህረ ምርጫ ሥራዎቻችን በውጤታማነት በመከወን የያዝናቸውን ግቦች በተሟላ መልኩ ከማሳካት አንፃር የተገኙ ዉጤቶችን ከመላው የከተማችን አመራሮች ጋር ገምግመናል ብለዋል።
7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዳይጠናቀቅ ለማደናቀፍ በውጭም በውስጥም በጋራ በማበር በሚደያ ዘመቻዎች እና በተለያዩ ቅስቀሳዎች ሰላም የማደፍረስ ዝግጅቶችና ትንኮሳዎች ሳይሳኩ መክነው መቅረታቸውንም ነው ከንቲባዋ ያወሱት።
በኢትዮዽያ ታሪክ ትልቅ እድገት የታየበት ዴሞክራስያዊ፣ ሰላማዊና ተዓማኒ ምርጫ በማካሄድ ኢትዮዽያዊን በፅናት አዲስ ታሪክ ፅፈው ኢትዮጵያ መርጣለች፣ ኢትዮጵያ አሸንፋለች።
እንደሃገር ያሳካነው እጅግ ውጤታማ እና ታሪካዊ ምርጫ የህዝባችን ፣የአመራራችን፣ የአባሎቻችን ፣የደጋፊዎቻችን፣የሲቭክ ማህበራት ፣ የሚድያዎቻችን፣ ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም በገለልተኝነትና በከፍተኛ ዲሲፕሊን ትልቅ ሃገራዊ ሃላፊነታቸዉን የተወጡት የፀጥታ አካላትና የምርጫ ቦርድ በጥቅሉ ሁሉም ባለድርሻ አካል እንደ ሀገር ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላንን ቁርጠኝነትና በጋራ ያሳካነው ግብ መሆኑን ተግባብተናል ። ለዚህም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት እናመሰግናለን።
የድህረ ምርጫ ስራዎቻችን በውጤታማነት በመፈፀም ይህንን ፅኑ ህዝብ ለመካስ ያስቀመጥናቸዉን ግቦች በተሟላ መልኩ ለማሳካት ከመላው አመራራችን ጋር ተግባብተናል።