Search

የቱለማ ገዳ ሥርዓት የ71ኛው ዙር የሥልጣን ሽግግር ነገ ይፈጸማል

ቅዳሜ ሰኔ 06, 2018 54

የቱለማ ኦሮሞ ገዳ ሥርዓት የ71ኛው ዙር የስልጣን ሽግግር 'ዳካ ኮራ' በተባለ ልዩ ስፍራ እየተካሄደ ይገኛል።

የሥልጣን ርክክቡ ማጠቃለያ በነገው ዕለት 'ዳካ ኮራ' በተባለ ልዩ ስፍራ የስልጣን ወይም የአለንጋ ሽግግር መርሐ ግብር የተለያዩ አካላት በተገኙበት ይካሄዳል።

የገዳ ሥርዓት ለብዙ ዘመናት የዘለቀ እና ዓለም ያደነቀው የማይዳሰስ ቅርስ ሲሆን፤ የማኅበረሰቡን ባህል፣ እሴትና ሥነ-ምግባር ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ በማሻገር ረገድ ትልቅ ሚና እየተወጣ ነው።

ገዳ፤ ሰላም እና እርቅን የሚያሰፍን፣ የማኅበረሰቡን ተሳትፎ የሚያጠናክር፣ ማንነትን እና ባህልን የሚጠብቅ፣ እኩልነትን የሚያረጋግጥ እንዲሁም ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግርን ለትውልድ የሚያስተምር ሥርዓት ነው።

የቱለማ ገዳ ሥርዓት የ71ኛውን ዙር የሥልጣን ሽግግር ከ'ገዳ ሜልባ' ወደ 'ገዳ ሙደና' ለማስተላለፍ የተለያዩ ባህላዊ ሥነ-ሥርዓቶች በ'ዳካ ኮራ' የባህል ስፍራ እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በዚህ ሥርዓት ላይ ሥልጣን ለሚረከቡት አካላት ቦኩ ወይም የሥልጣን ማሳያ የሆነው በትር እና አለንጋ ይረከባሉ።

በሥልጣን ሽግግሩ ባህላዊ ሥርዓት ላይ ግብዣዎች፣ ምርቃት፣ ባህላዊ ዜማዎች እና ውዝዋዜዎች የሚቀርቡ መሆኑን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።