Search

ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ጥበቃ ረገድ ጠንካራ ራዕይ እና አመርቂ አፈጻጸም አላት - ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

ማክሰኞ ሰኔ 16, 2018 52

ቻተም ሃውስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ተቋም በለንደን ባዘጋጀውና በተከፋፈለ ጂኦ-ፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ የኮፕ ጉባኤዎችን አስፈላጊነት ማጉላት በሚል ርዕስ በተካሄደው የአየር ንብረት ሳምንት የውይይት መድረክ ላይ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ32 ተሰያሚ ፕሬዚዳንት የሆኑት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (/) የኮፕ30 ፕሬዚዳንት አንድሬ ኮሬያ ከብራዚል፣ እንዲሁም የኮፕ31 የወከሉት የቱርክዬ የአካባቢ፣ የከተማ ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር በተገኙበት ውይይቱ ተካሂዷል።

ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ጥበቃ ረገድ ያላትን ጠንካራ ራዕይ እና አመርቂ አፈጻጸም ያነሡት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (/) በተለይም ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ በፖሊሲ ተደግፈው ተግባራዊ የተደረጉ አፈጻጸሞችን አጽንዖት ሰጥተው አብራርተዋል።

አክለውም፣ ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው የኮፕ32 ቀዳሚ ተግባራት፣ በቱርክዬ እና አውስትራሊያ በጋራ ከሚዘጋጀው የኮፕ31 ከተገኙ ውጤቶች በመነሣት ቀጣይነትን ማረጋገጥ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ይህ አካሄድ ደግሞ ከእኛ በፊት ከነበሩት ጋር በቅንጅት በመሥራት የጋራ ተግባራትን ማጠናከር እና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያዊ ሒደት ላይ ያለውን ተስፋ መልሶ ማቀጣጠል የሚለውን መደመር መርሕ እንደሚያንጸባርቅ አጽንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።