Search

ኢቢሲ መሰረታችንን የሰራ ሚዲያ ነው - የሙዚቃ ባለሙያው ሰርጸ ፍሬስብሀት

Aug 14, 2025

ኢቢሲ በራሱ አቅም ያበለጸገውን የሞባይል መተግበሪያ በትናትናው እለት በይፋ  አስመርቆ ወደ አገልግሎት አስገብቷል።

በዚህ ሁነት ላይ የተገኘው የሙዚቃ ባለሙያው ሰርጸ ፍሬስብሀት በሰጠው አስተያየት፤ ኢቢሲ የብዙዎቻችንን መሰረት የሰራ ሚዲያ ነው ሲል ገልጿል።

በዘጠናዎቹ በኢቢሲ የሚተላለፈው የኢትዮጵያ አይዶል ሲያመልጠኝ እስኪደገም ጠብቄ ነበር የማየው ሲልም ትዝታውን ያጋራል፡፡

ኢቢሲ ከህዝብ ጋር እንድገናኝ እድል የፈጠረልኝ ተቋም ነው ያለው የሙዚቃ ባለሞያው፤ ሚዲያው በዲጂታል አማራጮች መቅረቡ ሰዎች በቀላሉ በተንቀሳቃሽ ስልኮች የሚፈልጉትን ፕሮግራም እንዲከታተሉ ይረዳቸዋል ብሏል፡፡

ኢቢሲ እንደቀዳሚነቱ የኢትዮጵያ አይዶልን ለሌሎች ምሳሌ በሚሆን መልኩ ማቅርቡንም ገልጿል።

በተለያየ አጋጣሚ ፕሮግራሙን በቴሌቪዥን መስኮት መመልከት ላልቻሉ በቀላሉ እጃቸው ላይ ባለ ስልክ እንዲያዩ ያበለፀገው የሞባይል መተግበሪያ ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ነው የተናገረው።

በሔለን ተስፋዬ

#EBC #ebcdotstream #Digital_EBC #DigitalEthiopia #EBCApp