የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ታሪካዊቷና ውቧ ከተማ ሊዮን የተጀመረው አዲሱ የበረራ መስመር መዳረሻውን ሲያደርግ ደማቅና ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎለታል።
ይህ አዲስ በረራ በይፋ መጀመሩን ተከትሎ ወደ ከተማዋ ያቀናው የመጀመሪያው በረራ በድምቀት ተስተናግዷል።
ወደ ፈረንሳይዋ ሊዮን ከተማ የሚደረገው ይህ አዲሱ በረራ በደማቅ ሁኔታ መጀመሩ፣ አየር መንገዱ በአውሮፓ ያለውን ተደራሽነት ይበልጥ የሚያሰፋና የደንበኞችን የጉዞ አማራጭ የሚያሰፋ ስኬት ነው።