Search

የአርሶ አደሩን ክብርና ምቾት ያረጋገጠው ዘመናዊው የሀማሳ ሞዴል መንደር ተመረቀ

ሓሙስ ሰኔ 25, 2018 73

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ79.4 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውንና የገጠር ኮሪደር ልማት አካል የሆነውን ዘመናዊውን የሀማሳ ሞዴል መንደር ዛሬ በይፋ መርቀዋል።

ይህ አዲስ የሞዴል መንደር ግንባታ የአርሶ አደሩን ኑሮ ይበልጥ ለማዘመንና ምርታማነቱን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ታስቦ የተገነባ ነው።

መንደሩ አርሶ አደሩን ከተለመደው አኗኗር በማላቀቅ፤ ዘመናዊ የመታጠቢያ ክፍሎች፣ የእንስሳት ማደሪያዎች፣ የጓሮ አትክልት ስፍራዎች፣ የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች የተሟሉለት በመሆኑ ለነዋሪዎቹ ሁለንተናዊ ብልጽግናን እንደሚያረጋግጥ ተገልጿል።

"ይህ ሞዴል መንደር የገጠሩን ማኅበረሰብ ክብር፣ ምቾት እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ የሪፎርማችን ሕያው ፍሬ ነው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፕሮጀክቱን ሀገራዊ ትርጉምና ፋይዳ ገልጸዋል።