Search

የሀገር ውስጥ ምርትን በራስ አቅም ማሳደግ የኢኮኖሚ ነጻነታችን እና የሉዓላዊነታችን መሰረት ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሓሙስ ሰኔ 25, 2018 60

የሀገር ውስጥ ምርትን በራስ አቅም ማሳደግ የኢኮኖሚ ነጻነት እና የሉዓላዊነት መሰረት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋሞ ዞን በመገኘት በወርሃ ነሐሴ 2017 ዓ.ም ሥራ የጀመረውን የ 'ዮ ሆልዲንግ’ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ ጎብኝተዋል።

ፋብሪካው የኢንዱስትሪዎችን ፍላጎት በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ከውጭ የሚገባውን ምርት ማስቀረት መቻሉን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤  በተጨማሪም ይህ የልማት ተቋም ለአካባቢው ነዋሪዎች ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠሩን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት በጠንካራ የሥራ ባህል በሀገር ውስጥ በማልማት፣ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ልዕልና የማረጋገጡ ጉዞ በተጠናከረ መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት አረጋግጠዋል።