Search

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለመቄዶኒያ የአምቡላንስና የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ቅዳሜ ሐምሌ 04, 2018 158

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለመቄዶኒያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የአምቡላንስ እና 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ።

የፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ማዕከሉን በቦታው ተገኝተው የጎበኙ ሲሆን፣ የተዘጋጀውን የአምቡላንስና የገንዘብ ድጋፍ አስረክበዋል።

ጉብኝቱና ድጋፉ የተደረገው 2016 . ጀምሮ በየዓመቱ ሐምሌ 4 ቀን በመቄዶኒያ "የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ቀን" ሆኖ መከበር መጀመሩን ተከትሎ ነው።

ማዕከሉ ሰዎችን ከወደቁበት ለማንሳትና ወደ ሕክምና ተቋማት ለመውሰድ የአምቡላንስ እጥረት እንደነበረበት የተገለጸ ሲሆን፣ የአምቡላንስና የገንዘብ ድጋፉም ክፍተቱን ለመሙላት የተፈጸመ መሆኑ ተገልጿል።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚህ ወቅት፣ ፌዴራል ፖሊስ ሀገርን በመስዋዕትነት ከመጠበቅና ሕዝብን ከማገልገል ባለፈ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።

የፌደራል ፖሊስ በየዓመቱ ሐምሌ 4 ቀን በመቄዶኒያ ዋና ማዕከል ብቻ ሳይሆን፣ በየክልሉ የሚገኙ ቅርንጫፎችን ጭምር በመሄድ እንደሚጎበኝና ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

የመቄዶኒያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራች ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው፣ ከኮሚሽኑ የተደረገላቸው ድጋፍ ተጨማሪ የተቸገሩ ሰዎችን ለመርዳት ትልቅ አቅም እንደሚሆናቸው ገልጸው ምስጋና አቅርበዋል።

መቄዶኒያ "ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው" በሚል መርህ አጋዥ የሌላቸውንና የተቸገሩ ወገኖችን ከጎዳና እያነሳ የመጠለያና የምግብ  አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በባዬ ሙላት

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: