Search

ከነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) ሕይወት ለሀገራችን የምንማረው ታላቅ ትምህርት

ሰኞ ነሐሴ 18, 2018 57

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በመውሊድ በዓል መልእክታቸው የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) ሕይወት ትውልድን ለበጎ የሚቀርጽ እና ለሀገር ግንባታ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ከነቢዩ ታሪክ የምንማራቸው 4 ዋና ዋና ነጥቦች፦

1. የተጠራንበትን ዓላማ ማክበር፦ ነቢዩ የተጠሩበት ዓላማ ታሪክን መቀየር እና ትውልድን መቅረጽ መሆኑን አምነው በቃላቸውና በሥራቸው አክብረውታል። እኛም ለሀገር ዓላማ ከተጠራን በቃላችንና በሥራችን ልንገልጸው ይገባል።

2. ለዓላማ ዋጋ መክፈል፦ ነቢዩ ከቦታቸው ተስድደዋል፣ ፈተናዎችን አልፈዋል፣ ነገር ግን በአላህ ኃይል አሸንፈዋል። ክብር ያለ መከራ አይገኝም እና ለዓላማችን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆን አለብን።

3. ያመንንበትን ለሌሎች ማካፈል፦ መልእክቱን ለራሳቸው ብቻ አላስቀሩም፤ ለዓለም አዳርሰዋል። እኛም የያዝነውን በጎ ዓላማ ሌሎች እንዲያውቁትና እንዲያምኑበት መትጋት አለብን።

4. ለሀገር ግንባታ መጠቀም፦ በዓሉን ስናከብር ከሕይወታቸው እየተማርን፣ የተማርነውን ለሀገረ መንግሥት ግንባታችን ልንጠቀመው ይገባል።

እንኳን 1501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም የመውሊድ በዓል!

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: