Search

ደቡብ ኮሪያ ወደ አውሮፓ የሚወስደውን አዲሱን የአርክቲክ የባሕር ንግድ መስመር በሙከራ ደረጃ ለመጠቀም ታሪካዊ ጉዞ ጀመረች

እሑድ ነሐሴ 17, 2018 105

በዓለም አቀፍ የባሕር ትራንስፖርት ዘርፍ ትልቅ አቅም ያላት ደቡብ ኮሪያ፣ የቡሳን ወደቧን የዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል ለማድረግና ወደ አውሮፓ የሚደረገውን የጭነት ጉዞ የሚያሳጥር አዲስ አማራጭ መስመር በስኬት ለመፈተሽ የሚያስችላትን የመጀመሪያውን የንግድ መርከብ ጉዞ በይፋ አስጀምራለች።

«ፓንስታር አክሮ» (PanStar Acro) የተሰኘችውና 2 ሺህ 758 መደበኛ ባለ 20 ጫማ ኮንቴነሮችን የመሸከም አቅም ያላት ግዙፍ የኮንቴነር መርከብ፣ በምሥራቅ ሩሲያና በቤሪንግ ባህር አድርጋ በሰሜናዊው የአርክቲክ የበረዶ መስመር በኩል ወደ ብሪታንያ፣ ኔዘርላንድስ እና ፖላንድ የምታደርገውን 40 እስከ 45 ቀናት ጉዞ ጀምራለች።

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት -ምዮንግ የአርክቲክ የባሕር ትራንስፖርት ልማትን የሀገሪቱ ዋና የኢኮኖሚ ትኩረት በማድረግ እስከ ... 2030 ድረስ መስመሩን መደበኛ የንግድ መሸጋገሪያ ለማድረግ አቅደው እየሰሩ ይገኛሉ።

ይህ የዓለም አቀፍ የንግድ ትስስር አዲስ ተስፋ የፈነጠቀበት የባሕር መስመር፣ የመርከቦችን የጉዞ ጊዜና ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ ለዓለም አቀፍ ንግድ አስተማማኝ አማራጭ መውጫ በመሆን አዲስ የዘመናዊ ትራንስፖርት ምዕራፍ የሚከፍት ነው።

የመርከቧ አስተማማኝ ጉዞ እንዲረጋገጥና የበረዶ እንቅፋቶችን ለመሻገር ከሩሲያ ጋር አስፈላጊው የቴክኒክ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ የዓለም አቀፍ አየር ንብረት ለውጥና የበረዶዎች መቅለጥ የሰሜናዊውን መስመር ለባሕር ጉዞ ይበልጥ ምቹ እያደረገው መጥቷል።

ባለፈው ዓመት ብቻ 100 በላይ መርከቦች ይህንን የሰሜን የባሕር መስመር ለንግድ እንቅስቃሴ የተጠቀሙበት ሲሆን፣ የደቡብ ኮሪያ አዲሱ የሙከራ ጉዞም የመለዋወጫ ዕቃዎችንና ልዩ ልዩ ምርቶችን ጭኖ በስኬት ወደ አውሮፓ በማምራት ላይ ይገኛል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: