Search

“ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት፤ እንደ ፈጣሪ ፈቃድ በሁሉም አጀንዳዎቻችን ላይ መግባባት ላይ እንደርሳለን” ፦ ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ

እሑድ ሐምሌ 05, 2018 62

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ፣ ባለፉት አራት ዓመታት ሲከናወን የቆየው የዝግጅት ስራ ፍሬ በማፍራት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለታሪካዊ ምክክር በጋራ መቆሙን አበሰሩ።

ዛሬ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የሩጫ መርኃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሮፌሰር መስፍን፣ ከመላው ኢትዮጵያ እና ከውጭ አገራት የተውጣጡ 4,000 ተመካካሪዎች በከተማዋ ታድመው።

ከዚህ በፊት ለያይተው፣ አጋጭተው እና አስኮርፈው የቆዩትን ምክንያቶች በጋራ በመምከር ወደ ዘላቂ ሰላም ለመሸጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ በንግግራቸው ወቅት፣ ኮሚሽኑ በተለያዩ ክልሎች እና የፌደራል ተቋማት የተሰባሰቡትን ሀገራዊ አጀንዳዎች መሰረት በማድረግ፣ በቀጣዮቹ ሳምንታት የኢትዮጵያዊያን የጋራ መግባባት ምዕራፍ እንደሚከፈት አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ የሁሉም እንደመሆኗ፣ ለዛሬው ታሪካዊ ቀን እንድንደርስ የመከላከያ ሠራዊት፣ የሰላምና የደህንነት አካላት፣ የሲቪል ማህበረሰብ እና መላው የሀገር ተቋማት ላደረጉት የላቀ ድጋፍና ትብብር በኮሚሽኑ ስም ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ በሩጫ መርኃ ግብሩ ላይ ለተሳተፉ ሕጻናት፣ ወጣቶችና አረጋውያን መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ፣ ይህ የተባረከ ቀን ኢትዮጵያዊያን በጋራ በመምከርና በመመካከር በሁሉም ሀገራዊ አጀንዳዎቻቸው ላይ መግባባት ላይ የሚደርሱበት መነሻ እንዲሆን ያላቸውን ጠንካራ እምነትና ተስፋ ገልጸዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: