በአዲስ አበባ በስኬት የተጠናቀቀው ዓለም አቀፍ የፓርላማ ደህንነትና መረጃ ፎረም ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ጉብኝት አድርገዋል።
እንግዶቹ በቆይታቸው የሀገራችንን ጥንታዊና ዘመናዊ የዲፕሎማሲ ታሪክ እንዲሁም የቤተ-መንግሥቱን ታሪካዊ ይዘት የተመለከቱ ሲሆን፣ ስፍራው የኢትዮጵያን ጥንታዊ ሥልጣኔና የአፍሪካን የረጅም ዘመን የዲፕሎማሲ አሻራ የያዘ ሕያው ምስክር መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስታውሎት (AI) እና የተቋማት ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥታ መስራቷ፣ ፎረሙ ካነሳቸው የአፍሪካ አንድነትና የጋራ ደህንነት እሴቶች ጋር የሚጣጣምና ለስልታዊ ቁርጠኝነቷ ማሳያ መሆኑን መጠቆማቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል።
ከሐምሌ 3 እስከ 4 ቀን 2018 ዓ.ም "ለአፍሪካ የደህንነት ቀጣና የዲሞክራሲያዊ ቁጥጥር እና የደህንነት ትብብርን ማጠናከር" በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ ፎረም፣ የፓርላማ አባላትን፣ የደህንነት ባለሙያዎችንና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያሳተፈ ነበር።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: