Search

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ያቀረቧቸው 12ቱ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች፦

ሰኞ ሐምሌ 06, 2018 217

የኢኮኖሚ መረጋጋት እና የኑሮ ውድነትን ማቃለል፡- የከተማዋ ነዋሪ ቀዳሚ ጥያቄ የሆነውን የኑሮ ውድነት መቋቋም ዋነኛ የትኩረት ሥራ ይሆናል።

የሥራ ዕድል ፈጠራ፡- የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የሚመጡ ዕድሎችን በመጠቀም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሥራ አጥነት ምጣኔን መቀነስ።

የመሠረተ ልማት አስተዳደር፡- ባለፉት ዓመታት የተገነቡ ግዙፍ መሠረተ ልማቶችን እና የኮሪደር ልማቶችን መጠበቅና አገልግሎታቸውን በዘላቂነት ማስቀጠል።

የሀብት አያያዝና ጥገና፡- አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ጎን ለጎን የተገነቡ መንገዶችን፣ መናፈሻዎችንና መብራቶችን በጥራት የመያዝና የመጠገን ባሕል ላይ በጀት መመደብ።

የከተማ ውበትና ጽዳት፡- የተገነቡ የኮሪደር መስመሮች በጽዳትና በአረንጓዴነት እንዲቀጥሉ ከኅብረተሰቡና ከግሉ ዘርፍ ጋር የተቀናጀ አሠራር መዘርጋት።

ትራንስፖርት እና የትራፊክ ፍሰት፡- ከከተማዋ ፈጣን ዕድገት ጋር አብሮ የሚሄድ ቀልጣፋ የሕዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትና አስተዳደር ሥርዓትን ማጠናከር።

መልካም አስተዳደርና ዲጂታላይዜሽን፡- ብልሹ አሠራርን ለመቀነስ "አዲስ መሶብ" 50 በመቶ የደረሰውን አገልግሎት ወደ 100 በመቶ በማሳደግ አሠራሩን ሙሉ በሙሉ ማዘመን።

የማኅበራዊ ልማት ማጠናከር፡- የተማሪዎች ምገባና አልባሳት አቅርቦትን ማስቀጠል፤ እንዲሁም አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ።

የገቢ አሰባሰብና ፋይናንስ ዲሲፕሊን፡- ለዘላቂ ልማት የሚውሉ ገቢዎችን በአግባቡ መሰብሰብ፣ የታክስ መሠረቱን ማስፋት እና ቁጠባን ማረጋገጥ።

ሰላምና ጸጥታን ማረጋገጥ፡- የማኅበረሰብ አቀፍ የጸጥታ አደረጃጀቶችን በማጠናከር ወንጀልን መቀነስ፣ እንዲሁም ሕገ ወጥ የመሬት ወረራና ግንባታን በመከላከል የሕግ የበላይነትን ማስፈን።

የቤት ልማት ፕሮግራሞች፡- የነዋሪውን የቤት ጥያቄ ለመመለስ በመንግሥት፣ በግል ዘርፍና በሕብረት ሥራ ማኅበራት የቤት ልማትን በስፋት ማከናወን።

የውኃ እና የመንገድ ፕሮጀክቶች፡- የተጀመሩ ሜጋ የውኃ አቅርቦት ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ፣ እንዲሁም የመንገድ መሠረተ ልማትን በማስፋፋት ኔትወርኩን ማጠናከር።

በጠቅላላው፣ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ስሟና ግብሯ የተናበበ ስማርት ከተማ ለማድረግ የተጀመረው ልማት በጥራት፣ በስፋትና በፍጥነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማስታወቃቸውን ከአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: