Search

የባህር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱ ተርሚናል ቀልጣፋ አገልግሎት እንድናገኝ አስችሎናል - ተገልጋዮች

ሰኞ ነሐሴ 18, 2018 35

በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የባህር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱ ተርሚናል መንገደኞችን በአዲስ መልክ እያስተናገደ ይገኛል።

አዲሱ ተርሚናል ሰፋፊ የአውሮፕላን ማቆሚያዎችን፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሠረተ ልማቶችን እንዲሁም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን አሟልቶ የተገነባ ነው።

ኢቲቪ ያነጋገራቸው መንገደኞች ከዚህ በፊት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ነባሩ ተርሚናል የተጨናነቀ እና ባህር ዳርን የማይመጥን እንደነበረ ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ የተገነባው አዲሱ ተርሚናል ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንድናገኝ አስችሎናል ሲሉ መንገደኞቹ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ባህር ዳር ከተማ ጣና ሐይቅን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች እና ተፈጥሯዊ መስህቦች መገኛ እንደመሆኗ፣ የአየር ትራንስፖርት አቅሟ መጠናከር የጎብኚዎችን ፍሰት በመጨመር ለኢኮኖሚው ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክት ስለመሆኑም ገልጸዋል።

በተጨማሪም ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት እና ለኮንፍረንስ ቱሪዝም ዕድገት ተጨማሪ አቅም በመፍጠር ከከተማዋ አልፎ ለክልሉ ተወዳዳሪነት ሚና የሚጫወት ስለመሆኑ አክለዋል።

ከተማዋ በግጭት ምክንያት ጉዳት አስተናግዳ እንደነበር አስታውሰው፣ የአዲሱ ተርሚናል መገንባት የመደመር መንግሥት ሰላምን ከማስፈን ጎን ለጎን የሕዝብን ተጠቃሚነት ለሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች ትኩረት መስጠቱን ያሳያል ብለዋል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: