Search

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የሰኔ 15ቱ የከፍተኛ አመራሮች ግድያ አንዳች ግብ ያላሳካ መጥፎ ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዓርብ ሐምሌ 24, 2018 65

በሰኔ 15 ቀን 2011 . በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ የተከሰተው አሳዛኝ ድርጊት በስሑት የመረጃ ግምገማ እና በሁለት እግር ለማንከስ በተደረገ የፖለቲካ ስሌት የተከሰተ ጥቁር ጠባሳ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሚኮ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በወቅቱ ያጋጠመውን ሁኔታ ሲያብራሩ ድርጊቱ ለሀገር ለውጥ ከፍተኛ ሚና የነበራቸውን እንደ ዶክተር አምባቸው እና ጄኔራል ሠዓረ ያሉ ቁልፍ የለውጥ ኃይሎችን ያሳጣ፣ በፖለቲካ አመራሩ መካከል የነበረውን መተማመን ያቀዘቀዘ እና በኃይል ሥልጣን ለመያዝ የሚደረግን አጥፊ የፖለቲካ ባሕል ያስቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንም ድረስ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እያንዣበበ ያለውን አደገኛ የትርክት ስብራት አጥብቀው ኮንነዋል።

ገዳይም ሟችም በእኩል ደረጃ በጀግንነት የሚወደሱበት ሁኔታ አደገኛ የፖለቲካ ብዥታ መሆኑን ጠቅሰው፣ ታሪክን እያንሻፈፉ እና እየመረጡ ማቅረብ የነገውን ትውልድ ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ ታሪክ እንዳለ በትክክለኛው መንገድ መቀመጥ እንዳለበት አሳስበዋል።

የሰኔ 15ቱን ክስተት አስመልክቶ በወቅቱ ስለተሰጠው መግለጫ ሲራገቡ የነበሩት የሴራ ትንተናዎችም እውነቱን ለመቅበር የሞከሩ መሆኑን ጠቅሰው፣ ድርጊቱ ከጅምሩ ምንም ግብ ያላሳካ እና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጠባሳነቱ የሚታወስ ዘግናኝ አጋጣሚ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በበረከት ሽመልስ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: