Search

የሕዝብ ከፍተኛ ተስፋ እና የተመካካሪዎች ቁርጠኝነት ሀገራዊ ምክክሩን ወደ ስኬት እየመራው ነው - ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

ዓርብ ሐምሌ 24, 2018 79

እየተካሄደ ባለው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዙሪያ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በሰጡት መግለጫ፣ የሕዝቡ ከፍተኛ ተስፋ እና የተመካካሪዎች ቁርጠኝነት ሂደቱን ወደ ስኬት እየመራው መሆኑን ገልጸዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው እንዳመላከቱት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ያለው ተስፋ እጅግ ከፍተኛ ነው።

የዚህ ተስፋ ዋና ማዕከል ደግሞ ሰላም፣ መብትን ማስከበር እንዲሁም ለዘመናት ወደ ጭቅጭቅ፣ ግጭት እና ጦርነት ሲወስዱ የነበሩ መሠረታዊ አጀንዳዎችን በትክክል ተነጋግሮ አቅጣጫ ማስቀመጥ መቻሉ እንደሆነ አብራርተዋል።

ተመካካሪዎቹ እጅግ የሚጋጩ እና ፅንፍ ሊይዙ የሚችሉ ሀሳቦችን ይዘው ቢመጡም፣ በተቻላቸው መጠን ወደ መሀል ለመምጣት እና የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት እጅግ የሚያስደንቅ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።

ይህ ወደ አንድ ሀሳብ የመምጣት ሂደት ከማንም በላይ ሀገርን ማስቀደም እንደሆነ በመገንዘብ የተደረገ መሆኑንም አክለዋል።

ቀደም ሲል አብዛኛው ተሳታፊ የራሱን አካባቢ እና የጠበበ ጥያቄ ብቻ ይዞ ይመጣ እንደነበር ያሱት ፕሮፌሰር መስፍን፣ አሁን ግን በሂደት በጋራ የመደማመጥ እና "የጋራ ማንነታችን ይከበር" ወደሚለው አቃፊ አስተሳሰብ መሸጋገራቸውን ገልጸዋል።

በሐና ምንዳሁን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: