የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የጀመረውን ሀገራዊ የምክክር ሂደት ተዓማኒነቱን ባስጠበቀ እና አሳታፊ በሆነ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ።
ኮሚሽኑ የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት በገለልተኝነትና በግልጽነት እየተወጣ እንደሚገኝ ዋና ኮሚሽነሩ በሰጡት መግለጫ ጠቁመው፣ የምክክር መድረኮቹ ሁሉንም ድምፆች በማስተናገድ ረገድ አዎንታዊ ውጤቶችን እያሳዩ መሆናቸውን አብራርተዋል።
በስልታዊ ቡድኖች ደረጃ የተነሱ ሐሳቦችን አጥርቶ ለመሄድ ሰፊ ጥረት መደረጉን ገልጸዋል።
በባለድርሻ አካላት መካከል በአንዳንድ ቡድኖች ላይ ውይይቱ በፍጥነት የተከናወነ ሲሆን፣ በሌሎች ቡድኖች ደግሞ ሐሳቦችን በበለጠ ዝርዝር የማጥራት ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
አክለውም፣ የ500 አባላት ውይይት ነገ ሊጀምር እንደሚችል አመላክተዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: