የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ ፋግታ ለኮማ ወረዳ ነቸላ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራን አስጀምረዋል።
በወረዳው ነቸላ ቀበሌ የተጀመረውን የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚያከናውነው ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በዚሁ ወቅት ገልጸዋል።
የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ የአኗኗር ዘይቤ በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
አገው ምድር የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የአረንጓዴ የልማት ተምሳሌት መሆኑን ጠቅሰው፤ “በተለይምፅንፈኝነትን በማሸነፍ ሰላሙን ጠብቆ ለልማት በቆመው የነቸላ ቀበሌ ማህበረሰብ መካከል በመገኘቴ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል።
ብሔራዊ ባንኩ ደረጃቸውን የጠበቁ እና ሞዴል የሚሆኑ የገጠር መኖሪያ ቤቶችን በአጭር ጊዜ ገንብቶ ለማጠናቀቅ በቂ በጀት ይዞ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸዋል።
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው በበኩላቸው፥ ነቸላ ቀበሌ ሰላሟን አስጠብቃ የዘለቀች መሆኗን አንስተው፤ የፀናው ሰላሟም ልማትን ማምጣቱን አክለዋል።
በቀበሌዋ የገጠር ኮሪደር ልማቱን በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማከናውን ሥራውን ዛሬ ላስጀመረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክም ምስጋና አቅርበዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: