Search

ከ20 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የተሳካ የጎዳና ላይ ሙከራ ያደረገው የቻይናው አሽከርካሪ አልባ ታክሲ

Aug 19, 2025

 

የቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ባይዱ ስሪት የሆነው አፖሎ ጎ የተሰኘው አሽከርካሪ አልባ መኪና ከእክል በፀዳ ሁኔታ ከ 20 ሺህ ኪሎ ሜትሮች በላይ መጓዝ መቻሉ ተገልጿል።

የቻይና ጎግል በመባል እውቅ የሆነው ኩባንያው የሰው አልባ ተሽከርካሪ ሀሳቡን እ.አ.አ በ2017 ነበር ይዞ ብቅ ያለው።

ይህንንም በማጎልበት እ.አ.አ በ2019 የሮቦት ታክሲ ሀሳብን በማምጣት ፈር ቀዳጅ ለመሆን መብቃቱ ተነግሯል።

በዚህ መልኩ የፈጠራ ስራውን እያሳደገ የመጣው ባይዱ፧ መሪው በስተቀኝ የተገጠመለት አሽከርካሪ አልባ የሮቦት ታክሲ ንድፈ ሀሳቡ ፈቃድ ያገኘለት የመጀመሪያ የቻይና  ኩባንያ ነው።

ከሰሞኑም ኩባንያው በአርፊሻል ኢንተለጀንስ የተጋዘውን አሽከርካሪ አልባ ታክሲ የ20 ሺህ ኪሎ ሜትር የተሳካ የጎዳና ላይ ሙከራ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ኩባንያው ከዚህ በተጨማሪም 10 ተሽከርካሪዎችን በሆንግ ኮንግ ሰሜናዊ ክፍል ላንታው እና ቱንግ ቹንግ በተሰኙ አካባቢዎች የሙከራ ጉዞ ማድረጉ ተጠቅሷል።

አሁን ላይ የተደረገው ሙከራ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች ከቻይና ባለፈ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የበለጠ ተቀባይነት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን የዘገበው ሳውዝ ሞርኒግ ፖስት ነው።

በአፎምያ ክበበው

#ebc #ebcdotstream #Robotaxi #technology