Search

አዲስ አበባ ለሁሉም ነዋሪዎቿ በእኩልነት ያበረከተችው ድንቅ ስጦታ - አራዳ ፓርክ

ማክሰኞ ነሐሴ 12, 2018 124

የመዲናችን አዲስ አበባ ውበትና ዘመናዊነት በየዕለቱ እያደገ በሄደበት በዚህ ወቅት፣ በከተማችን እምብርት የተገነባው ውቡ አራዳ ፓርክ ለሁላችንም የተበረከተ ድንቅ የጋራ መገልገያ ስፍራ ሆኖ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ይህ ፓርክ ማንኛውንም የማህበረሰብ ክፍል በነፃ እና በእኩልነት ለማስተናገድ ታስቦ የተገነባ አካታች የህዝብ መዝናኛ ስፍራ ነው።

ይህ አረንጓዴ እና ዘመናዊ የመዝናኛ ስፍራ ለአዛውንቶች ሰላማዊ የእረፍት ጊዜን፣ ለወጣቶች እና ለተማሪዎች የመነቃቃት እና የፈጠራ ቦታን፣ ለህፃናት ደግሞ አስተማማኝ የጨዋታ ስፍራን ያዘጋጀ ነው።

በተጨማሪም ፓርኩ ለስፖርተኞች ለሰውነት ማጎልመሻ፣ ለአርቲስቶች ለኪነ-ጥበባዊ ስራዎቻቸው መነሻ እንዲሁም ለነጋዴው ማህበረሰብ ምቹ የመንፈስ ማደሻ ሆኖ ያገለግላል።

ከህዝብ መዝናኛነቱ ባለፈ አራዳ ፓርክ ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ እና የከተማችንን የቱሪዝም ፍሰት በማሳደግ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ታላቅ ፕሮጀክት ነው።

አዲስ አበባን የሁሉንም ነዋሪዎች ፍላጎት ባማከለ መልኩ ዘመናዊ እና ለኑሮ ምቹ አድርጎ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት፣ አራዳ ፓርክ ትልቅ ማሳያ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤም፥ «ኑ፣ ጊዜያችሁን ከቤተሰባችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር በውቡ አራዳ ፓርክ በጥሩ ሁኔታ አሳልፉ» ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: