Search

መታወቅ፦ የጸናች ሀገር መገለጫ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ዋና መሠረት

ረቡዕ ነሐሴ 13, 2018 79

 

መታወቅ የሰው ልጅ ሕልውና እና የመብቶቹ ሁሉ መነሻ ነው። በአንድ ሀገር ውስጥ ደግሞ የዜጎች ሕጋዊ እና አስተማማኝ ማንነት መረጋገጥ የጸናች ሀገር መገለጫ የመሆኑን ያህል፣ ለዲጂታል ኢኮኖሚ እና ተቋማዊ ዕድገትም ዋና መሠረት ነው።

ኢትዮጵያ ወደተሟላ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገው ጉዞ ያለ አስተማማኝ የመታወቂያ ሥርዓት እውን ሊሆን አይችልም።

ባለፉት ዘመናት የዜጎችን ሕጋዊ ማንነት ለማረጋገጥ በስፋት ሲያገለግል የቆየው የቀበሌ መታወቂያ፣ በመላ ኢትዮጵያ ባሉ 16 ሺህ የዝቅተኛ እርከን የአስተዳደር መዋቅሮች የሚሰጥ እና እንደ ፓስፖርት ማውጣት፣ የባንክ ሒሳብ መክፈት እንዲሁም በምርጫ ድምፅ መስጠትን ላሉ መሠረታዊ መብቶች መገልገያ ሆኖ ቆይቷም።

ይሁን እንጂ ማዕከላዊ የምዝገባ ሥርዓት የሌለው፣ የአንዱን መታወቂያ ከሌላው ለይቶ ማረጋገጥ የማይቻልበት እና በቀላሉ ለሐሰተኛ እና ሕገ ወጥ አሠራሮች የተጋለጠ መሆኑ የዜጎችን ደኅንነትም ሆነ የተቋማትን አሠራር ለከፍተኛ ስጋት ሲዳርግ ቆይቷል።

ከዚህ ባሻገር የግብር መታወቂያ (ቲን) ፓስፖርት፣ የመንጃ ፈቃድ እና የልደት ምስክር ወረቀቶችን ጨምሮ የነበሩት ልዩ ልዩ አሠራሮች ከሕዝቡ ከግማሽ በታች የሚሆነውን ብቻ የሚሸፍኑ እና በተበታተነ መዋቅር የተቃኙ በመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ ወደተቀናጀ የዲጂታል ምኅዳር የምታደርገውን ሽግግር ሲያደናቅፉት ኖረዋል።

ይህን ሥር የሰደደ ተደራሽነት እና የአስተማማኝነት ክፍተት ለመቅረፍ የተዘረጋው ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የኢትዮጵያን ዲጂታል ሽግግር በጽኑ መሠረት ላይ ያቆመ ዋና መልሕቅ ሆኖ እየተተገበረ ይገኛል።

2015 . በአዋጅ ቁጥር 1284/2015 ሕጋዊ ማዕቀፍ አግኝቶ ወደ ሥራ የገባው ፋይዳ፣አንድ ሰው፣ አንድ ማንነትበሚል መርሕ የዜጎችን የባዮሜትሪክ እና ዲሞግራፊክ መረጃ በማቀናጀት ፍጹም ታማኝ እና ልዩ የሆነ መለያ ቁጥር ይሰጣል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) እንደገለጹት፣ ፋይዳ የካርድ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) 7 በመቶ የማሳደግ አቅም ያለው፣ የግል መረጃ ምሥጢራዊነትን የሚጠብቅ እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ የመተማመኛ ሥርዓት ነው።

እስካሁን ወደ 50 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን መዝግቦ 150 በላይ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ጋር የተሣሠረው ይህ ሥርዓት፣ እስከ 2020 . ድረስ የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ወደ 115 ሚሊዮን ለማድረስ በመጓዝ ላይ ይገኛል።

ይህ እንቅስቃሴ በተለይም ቀደም ሲል ከአገልግሎቶች ተገልለው የነበሩ ሚሊዮኖችን ወደ መደበኛው የፋይናንስ ሥርዓት በማስገባት፣ የባንክ እና የሞባይል ገንዘብ ዝውውርን በማፋጠን እና የቢዝነስ እንቅስቃሴዎችን በማቀላጠፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው።

በተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት ግቦች እና በአፍሪካ ኅብረት አጀንዳ 2063 የተቀመጠውንበሕግ የታወቀ ማንነት ለሁሉምየሚለውን ዓለም አቀፋዊ ራዕይ መሠረት ያደረገው ፋይዳ፣ የጾታ እኩልነትን፣ የማኅበራዊ ጥበቃ አቅርቦትን እና የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ መሣሪያ ነው።

ፋይዳ ሐሰተኛ አሠራሮችን እና ማጭበርበርን በማስቀረት ተቋማዊ አሠራርን ግልጽ ከማድረጉም በላይ፣ ኢትዮጵያ በጽኑ መሠረት ላይ የቆመች፣ የዜጎቿ ማንነት እና ደኅንነት የተከበረባት ሀገር ሆና እንድትቀጥል የሚያስችል የዘመናችን መሠረታዊ መሠረተ ልማት ነው።

በሰለሞን ገዳ

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: