የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ይህንን የገለጹት፤ ዕዙ በብላቴ ማሰልጠኛ ማዕከል ልዩ ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የ45ኛ ዙር 'ጽናት' ኮርስ ኮማንዶ ሠልጣኞችን ባስመረቀበት ወቅት ነው።
በምረቃ መርሐ-ግብሩ ላይ ዋና አዛዡ እንደተናገሩት፤ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ወታደራዊ ዝግጁነቱንና የማስፈጸም አቅሙን ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ ይገኛል። ዕዙ “በየትኛውም ቦታና ጊዜ ከመንግሥት፣ ከሕዝባችንና ከተቋማችን የሚሰጠንን ማንኛውንም ግዳጅ ከትናንት በላቀ ደረጃ ለመወጣት ጠላቶች ከሚገምቱት በላይ ዝግጁ ነን” ብለዋል።
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ የተሰጡትን ታላላቅ ሀገራዊ ግዳጆች ሁሉ በላቀ ድል እየፈጸመ የመጣ ጠንካራ ኃይል መሆኑን ያነሱት ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ፤ ዕዙ በአስቸጋሪ ወቅትና ሁኔታዎች ከፊት በመሰለፍ እናት ሀገሩንና ሕዝቡን ከተጋረጠበት አደጋ መታደጉንም አስታውሰዋል።
ዛሬ ላይ ዕዙ ታሪኩን ጠብቆ ለመጓዝና ራሱን ለበለጠ ሀገራዊ ግዳጅ ለማዘጋጀት፤ ዘመኑን በዋጀ መንገድ ለኢትዮጵያ የሚመጥኑ ልዩ ኃይሎችን በላቀ ደረጃ እያበቃ እና አቅሙን እያጠናከረ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
በወንድወሰን አፈወርቅ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: