Search

የፕሪሚየር ሊጉ የምንጊዜም 10 ድንቅ አሰልጣኞች

ረቡዕ ነሐሴ 20, 2018 44

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተወዳጅ እና በየሳምንቱ ተናፋቂ እንዲሆን ዋንኞቹ ምክንያቶች የሚመዘገቡት ውጤቶች፣ የተጫዋቾች ክህሎትና ችሎታ እንዲሁም የሚቆጠሩ ግቦች ማራኪነት ብቻ አይደሉም።

ከአሸናፊነታቸው ጎን አሰልጣኞች በየጨዋታዎቹ ይዘው የሚገቡት ታክቲክ፣ የሚከተሉት ፍልስፍና እና እስከ መጨረሻዋ ፊሽካ ድረስ የሚጓዙበት የማይበገር የአሸናፊነት መንፈስ ዋናው ምክንያት ነው።

በዚህ መሠረት በዋንጫ ብዛት፣ በታክቲክ አብዮት እና በሊጉ ላይ ባሳረፉት ጥልቅ አሻራ የሊጉን ታሪክ የቀየሩ አስር አሰልጣኞች በእግር ኳስ ቤተሰቡ ዘንድ ልዩ ቦታ እንዳላቸው ቢቢሲ አስነብቧል።

1. ሰር አሌክስ ፈርጉሰን

ፈርጉሰን 1992/93 እስከ 2012/13 ድረስ 13 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር አሳክተዋል። ለሁለት አስርት ዓመታት የማንቸስተር ዩናይትድን የበላይነት በማረጋገጥ በታሪክ ቁጥር አንድ አሰልጣኝ ናቸው።

ከኤሪክ ካንቶና እስከ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ከዌይን ሩኒ እስከ ካርሎስ ቴቬዝ ድረስ ፈርጉሰን የዩናይትድን ቡድን ገንብተዋል። 13 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችም በሊጉ ታሪክ የማይነካ ክብረወሰን ይዘው ይገኛሉ።

2. ፔፕ ጓርዲዮላ

የእንግሊዝ እግር ኳስን በአጨዋወት መንገድ ከቀየሩ አሰልጣኞች መካከል ቀዳሚው የታክቲክ አብዮተኛ ናቸው።

ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ያሸነፉት ጓርዲዮላ፣ 2017/18 100 ነጥብ ድል በማስመዝገብ ታሪክ ሠርተዋል። ከዚያም ሲቲን በተከታታይ አራት ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ያደረጉ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ሆነዋል።

3. አርሰን ቬንገር

የእንግሊዝን እግር ኳስ ከሜዳ ላይ ታክቲክ በላይ በሆነ መልኩ የቀየሩ አሰልጣኝ ናቸው። አርሰናልን 1998 2002 እና 2004 የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን አድርገዋል።

ከሁሉም የሚለየው 2003/04 “Invincibles” ዘመን ነው። አርሰናል በዚያ የውድድር ዘመን አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ የሊጉን ዋንጫ አንስቷል።

ቬንገር ከአሰልጣኝነታቸው በተጨማሪ የአመጋገብ እና የልምምድ ስርዓትን በማዘመን የእንግሊዝን እግር ኳስ ባሕል የለወጡ ሊቅ ናቸው።

4. ጆዜ ሞሪንሆ

ስፔሻል ዋንበመባል የሚታወቁት ጆዜ ሞሪንሆ በቼልሲ ሦስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን አሳክተዋል።

2004/05 በመጀመሪያው ዓመት የፕሪሚየር ሊጉ ቆይታቸው፤ ቼልሲ 12 ነጥቦች ልዩነት ዋንጫ ሲያነሳ ቡድኑ 38 የሊግ ጨዋታዎች 15 ግቦች ብቻ የተቆጠሩበትን የማይደፈር የተከላካይ መስመር ገንብተዋል።

5. የርገን ክሎፕ

የሊቨርፑልን 30 ዓመታት የዋንጫ ጥም የቆረጡ አሰልጣኝ ናቸው። በከፍተኛ ጫና እና በፈጣን ሽግግር የተገነባው የክሎፕ እግር ኳስ አጨዋወት ሊቨርፑልን በአውሮፓና በእንግሊዝ ሀያል እና አስፈሪ ቡድን አድርጎታል።

6. ክላውዲዮ ራኒየሪ

"5,000 1" የተባለውን የሌስተር ሲቲ ተአምር የመሩት ክላውዲዮ ራኒየሪ ከፕሪሚየር ሊጉ ድንቅ አሰልጣኞች መካከል ስድስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ውጤታማ አሰልጣኝ ናቸው።

7. ኬኒ ዳግሊሽ

ከሊቨርፑል ጋር ውድድሩ ፕሪሚየር ሊግ ከመሰኘቱ በፊት ታላቅ ስኬት ያስመዘገቡ ቢሆንም፣ በብላክበርን ሮቨርስ ያነሱት 1994/95 ዋንጫ በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ልዩ ቦታ አለው።

ዳግሊሽ ብላክበርንን ከሁለተኛ ዲቪዚዮን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ካሳደጉ በኋላ ቡድኑን ከኃያሉ ማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በመፎካከር ዋንጫውን አሳክተዋል። በዚህም ከሁለት የተለያዩ ክለቦች ጋር የእንግሊዝ የሊግ ዋንጫ ካሸነፉ አሰልጣኞች መካከል አራተኛው ሆነዋል።

8. ሮቤርቶ ማንቺኒ

ማንቸስተር ሲቲን ለመጀመሪያው የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ያበቁ የማይረሱ አሰልጣኝ ናቸው።

2011/12 የውድድር ዘመን ዋንጫ በተለየ ሁኔታ የተገኘ ነበር። በመጨረሻው ሳምንት ሲቲ በጭማሪ ሰዓት ሁለት ግቦችን አስቆጥሮ የማይረሳውን የሻምፒዮንነት ድል አስመዝግቧል። የሰርጂዮ አጉዌሮ 94 ደቂቃ ግብ በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ከተመዘገቡ አይረሴ ግቦች መካከል አንዱ ነው።

9. ሚኬል አርቴታ

ሚኬል አርቴታ 2025/26 የውድድር ዘመን አርሰናልን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ በመምራት ለክለቡ የረጅም ጊዜ የዋንጫ ጥበቃ ማብቂያ አበጅቷል።

ከአርሰን ቬንገር 2004 Invincibles ዘመን በኋላ ዋንጫውን ያስገኘ የመጀመሪያው የአርሰናል አሰልጣኝም ሆኗል።

አርቴታ በተጨማሪም የሲቲ እና የሊቨርፑልን 8 ዓመታት የበላይነት በመስበር የመጀመሪያውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ በማንሳት የፕሪሚየር ሊጉ የምንጊዜም ቁጥር ዘጠኝ አሰልጣኝ ሆኗል።

10. ካርሎ አንቼሎቲ

በቼልሲ የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ዘመናቸው የሊጉን ዋንጫ ያነሱት ካርሎ አንቼሎቲ፣ ከምርጥ የፕሪሚየር ሊግ አሰልጣኞች መካከል 10 ደረጃን ይዘዋል።

ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ቼልሲን 2009/10 የውድድር ዘመን ፕሪሚየር ሊግን እና የኤፍ ዋንጫን በማሸነፍ ድርብ ድል አስመዝግበዋል።

በፕሪሚየር ሊጉ የእርስዎ የምንጊዜም ምርጥ አሰልጣኝ ማነው? ሀሳባችሁን አጋሩን።

በአዲስ የሺዋስ

@Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ  #PremierLeague #football #sports #ebcdotstream

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: