Search

በኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው 'የኦዳ ሙርቲ' ሥርዓት ዳግም ታደሰ

ረቡዕ ነሐሴ 20, 2018 39

'ኦዳ ሙርቲ' በምሥራቅ ቦረና ዞን መደ ወላቡ ወረዳ የሚገኝና ቀደምት የገዳ ሥርዓት ድንጋጌዎች የወጡበት ታሪካዊ ስፍራ ነው።

ቦታው አብሮነትን የሚያንጸባርቁ፣ የሰው ልጆችን መከባበር የሚያጎሉ፣ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተቆራኙና የእንስሳትን መብት ጭምር የሚያቀፉ ዘመናትን የተሻገሩ የገዳ ሥርዓት ሕግጋት የረቀቁበት መሆኑ ይነገራል።

ሆኖም በመደ ወላቡ 'ኦዳ ሙርቲ' ሕግጋት የሚደነገጉበት ይህ ሥርዓት ለበርካታ ዓመታት ተቋርጦ ቆይቷል።

በዛሬው ዕለትም ተቋርጦ የቆየውን ይህን ሥርዓት የማደስና መልሶ የመትከል ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

ሥርዓቱን ማደስ በገዳ ሥርዓት ውስጥ ያሉ ታላላቅ እሴቶችን ይበልጥ ለማጉላት እና ሀገራዊ ፋይዳቸውን ለማሳደግ እንደሚረዳ ተገልጿል።

በሥነ ሥርዓቱም ላይ አባ ገዳዎች፣ ሐደ ሲንቄዎች፣ የመንግሥት አመራሮች እና ከተለያዩ ዞኖች የተወጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

በአወል ሁሴን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: