Search

"የሀገር ብርታት ጥበብ ብልሃቱ ምክክር ነው"፦ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ

ቅዳሜ ነሐሴ 16, 2018 113

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያን አሸናፊነት የሚያረጋግጡ እና አንድነትን የሚያጸኑ የጋራ መሻቶች መገለጻቸውን ገልጸዋል።

ምክክሩ ለትውልድ የሚበጅ ጠንካራ ሐሳብ የተንሸራሸረበት ልዩ ቀን መሆኑን በማንሣት፣ ምክክር የሀገር ብርታት እንዲሁም የጥበብ እና ብልሃት መሠረት መሆኑን አስገንዝበዋል።

ፕሬዚዳንቱ በመልእክታቸው 130 ሚሊዮን ሕዝብን በመወከል 46 ቀናት በቆየው ውይይት ላይ የተሳተፉትን ተመካካሪዎች በልዩ ሁኔታ አመስግነዋል።

ተሳታፊዎቹ የአካባቢያቸውን መልካም ተሞክሮ በማምጣት ለኢትዮጵያ በሚበጅ መልኩ ማቅረባቸውን አድንቀው፣ ይኸው የሰላም ውይይት እንዲሳካ ላስቻሉ የመከላከያ ሠራዊት እና መላው የጸጥታ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪም ብሔራዊ ጥቅምን ያማከለ ምቹ የመወያያ መድረክ ላዘጋጁት የምክክር ኮሚሽኑ አባላት እና የዛሬ ሳንሆን የነገው ትውልድ ተስፋ እንድንሆን ላስቻሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ከፍ ያለ ዕውቅና ሰጥተዋል።

ፕሬዚዳንት ታየ ምክክር የነባር ባሕላችን አካል ቢሆንም ለፖለቲካ እና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ለማዋል ከዚህ ቀደም ተሞክሮ እንደማያውቅ አስታውሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) እንደዚህ ዓይነት የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ በቁርጠኝነት ኃላፊነታቸውን በመወጣታቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ውይይቱ ኢትዮጵያን አሸናፊ ለማድረግ የተወጠነ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፣ ጉባኤው የሁላችንንም ኢትዮጵያ የሚያጸና እና ለመጻኢው ዕጣ ፈንታ ብሩህ ተስፋ የፈነጠቀ መሆኑን አስረግጠዋል።

በለሚ ታደሰ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: