የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተሳታፊዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የእግር ጉዞ በኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት መንገዶች እያካሄዱ ነው።
ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ለመካፈል ከአህጉሪቱ 47 አባል ሀገራት የተወጣጡ የጤናና የፋይናንስ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ጤና ባለሙያዎችና የልማት አጋሮችን ጨምሮ ከ800 በላይ ተሳታፊዎች ናቸው ከዓድዋ መታሰቢያ ጀምሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የእግር ጉዞ እያካሄዱ የሚገኙት።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ጃናቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን እና የእግር ጉዞውን አስጀምረዋል።
ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት፣ በጤናው ዘርፍ የሚፈለገውን ግብ ለማሳካት ከንግግር ያለፈ ቁርጠኝነት አስፈላጊ በመሆኑ ኢትዮጵያ ቃልን ወደ ተግባር እየቀየረች መሆኑን አብራርተዋል።
በአካል ብቃት እንቅስቃሴው እና የእግር ጉዞው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞን ጨምሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን እና ታዋቂ ኤሌቶች ተገኝተዋል።
የቀጣናው የውሳኔ ሰጪዎች ይፋዊውን ስብሰባ ከመጀመራቸው አስቀድሞ፣ ውሳኔዎቻቸውን በተግባር ለማስደገፍ “Walk the Talk ቃልን በተግባር” በሚል በመሪ ሐሳብ የኮሪደር ልማት በተከናወነባቸው እና ለጤናና ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ ምቹ በሆኑ ጎዳናዎች የእግር ጉዞና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው።
በብሩክ ተስፋዬ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: