Search

የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን በማጽናት ሁለንተናዊ ስኬቶችን ማስቀጠል ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ረቡዕ ነሐሴ 20, 2018 235

በአማራ ክልል የተቋማትን የመፈጸም አቅም በማሳደግ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማላቅ አምራች እና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለመገንባት እየተሠራ ይገኛል።

"አርቆ ማየት፣ አልቆ መሥራት" በሚል መሪ ቃል የአማራ ክልል የ2018 በጀት ዓመት የአሻጋሪ ዕድገት እና ዘላቂ የልማት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በክልሉ በተቋማት ሪፎርም፣ በሀገራዊ ኢኒሼቲቮች ትግበራ እና በሁለንተናዊ የልማት ዘርፎች ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

ክልሉ በሥራ ዘመኑ በአሻጋሪ ዕድገትና ልማት ዕቅዱ የተመላከቱ መዳረሻ ግቦች ላይ ለመድረስ ለጋራ ራዕይ የሚታትር እና የጋራ ግብ ያለው አመራር ማረጋገጥ መቻሉንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

በ2019 በጀት ዓመት የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን በማጽናት ለውጤት እንዲበቁ ከማስቻል ባለፈ፣ ለአፈጻጸሙ ተግዳሮት የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ስልት መንደፍ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በራሔል ፍሬው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: