Search

የኅብረ ብሔራዊነቷ ትልቅነትና የታሪክ ምዕራፍ፦ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ያስተላለፉት መልዕክት

እሑድ ነሐሴ 17, 2018 118

 

የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት እና በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችው ሀገራዊ ምክክር ለመላው አፍሪካ ታላቅ ምሳሌ የሚሆን ታሪካዊ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል።
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ኦባሳንጆ፣ ለዚህ ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ መሳካት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሰላም የሁሉ ነገር መሠረትና ዋጋ ሊከፈልበት የሚገባ ታላቅ ሀብት መሆኑን ያሰመሩበት ኦባሳንጆ፣ ለ4 ዓመታት ዝግጅት ተደርጎበት ለ46 ቀናት በአራት ሺህ ተሳታፊዎች የተካሄደው ይህ ምክክር የሕዝቦችን የጋራ ድምፅና ሀገራዊ ሕልውና ለመስማት የተደረገ ታላቅ ጥረት መሆኑን ገልጸዋል።
ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚቻለው ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል ያካተተ ውይይት ሲኖር ብቻ መሆኑን ያብራሩት ኦባሳንጆ፣ በሂደቱ በቀጥታ ያልተሳተፉ ክፍሎች ካሉ በውጤቱ ትግበራ ወቅት ቦታ ሊሰጣቸው እንደሚገባ እና የተደረሱ ስምምነቶች በተግባር መተርጎም እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ያለፉትን የልዩነት እና የጥል ታሪኮች ወደ ጎን በመተው ወደ አዲስ የሰላም፣ የውህደትና የብልጽግና ምዕራፍ የምትሸጋገርበት ታሪካዊ ወቅት አሁን መሆኑንም አብራርተዋል።
በሐና ምንዳሁን

 

 

 

 

 

 

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: