Search

አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥነው ዘመናዊው «ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ» በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ሥራ ጀመረ

እሑድ ነሐሴ 17, 2018 92

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዘመናዊ የሕክምና ቴክኖሎጂዎችን ያሟላውን «ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ» መርቀው ሥራ ማስጀመራቸውን አስታወቁ።

ከንቲባዋ በመረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ አዲስ አበባን የምስራቅ አፍሪካ የጤና ቱሪዝም ማዕከል የማድረግ ታላቅ ራዕይ በመንግሥት ጥረት ብቻ ሳይሆን በግሉ ዘርፍ በሚደረጉ አጋዥና ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች ጭምር የሚሳካ ነው።

 ዛሬ ሥራ የጀመረው ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስም የዚሁ ሀገራዊ ራዕይ አካልና ተጨባጭ ማሳያ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

ይህ ግዙፍ የጤና ተቋም በሀገራችን ከላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀጥሎ ሁለተኛው PET-CT Scan Cath Lab እና ሌሎች ዘመኑን የዋጁ የተራቀቁ የሕክምና ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት የልህቀት ማዕከል መሆኑ ተጠቅሷል።

በጤናው ዘርፍ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ለዜጎች ሕይወት መታደግ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ፣ የከተማ አስተዳደሩ በዘርፉ ለሚሰማሩ የሕክምና ተቋማት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከንቲባዋ አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም ይህን ዘመናዊ የሕክምና ማዕከል እውን በማድረግ ለሀገራዊ የጤና እድገት የጎላ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ መስራችና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ኢማን አብዱልራህማን እና ባለቤታቸው አቡበከር መሐመድ ሳላህ፣ ከንቲባዋ በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: