Search

ዮሚፍ ቀጀልቻ የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረ

እሑድ ነሐሴ 17, 2018 111

ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በአርጀንቲና የተካሄደውን የቦነስ አይረስ ግማሽ ማራቶን ውድድር 56 ደቂቃ 51 ሰኮንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ዳግም አሻሽሏል።

ዮሚፍ ኡጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ በሊዝበን ያስመዘገበውን 57 ደቂቃ 20 ሴኮንድ የቀድሞ ክብረ ወሰን 29 ሰከንዶች አሻሽሏል።

ዮሚፍ ... 2024 ቫሌንሲያ ላይ 57 ደቂቃ 30 ሰኮንድ በመግባት ክብረ ወሰኑን ይዞ እንደነበር ይታወሳል። አትሌቱ በዓለም የግማሽ ማራቶን ንግስናውን በድጋሚ አረጋግጧል።

በተመሳሳይ በሴቶች የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፎይተን ተስፋይ ርቀቱን 1 ሰዓት 03 ደቂቃ 57 ሰኮንድ በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆናለች።

የዮሚፍ አዲሱ የዓለም ክብረ ወሰን የዓለም አትሌቲክስን ይፋዊ ማረጋገጫ የሚጠብቅ ይሆናል።

በእሱባለው ተሾመ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: