Search

የማታውቃቸውን 1ሺ 300 ወንጀለኞች ያስያዘችው ሰዓሊ

ረቡዕ ነሐሴ 14, 2017 94

ሎይስ ጊብሰን ትባላለች ከስዕል ሥራዋ ባሻገር ሞዴል ነበረች።

ዳንሰኛ የነበረችው ሎይስ በዩኒቨርሲቲም በመምህርነት አግልግላለች።

የፎረንሲክ ጥበብ ላይ ያተኮረ መፅሐፍም አሳትማለች።

21 ዓመቷ በሎስአንጀለስ በደረሰባት ፆታዊ ጥቃት እራሷን ለማጥፋት ሞክራ የነበረችው ሎይስ ወንጀለኞችን ለመያዝ በሚደረጉ ጥረቶች በስዕል ሥራዋ በመሳተፍ አንቱታን አትርፋለች።

ሎይስ ወደ ፓሊስ በመሄድ ምንም መረጃቸው ያልተገኙ እና ወንጀል ፈፅመዉ የተሰወሩ ተጠርጣሪዎችን ለምርመራ እንዲቀርቡ አደርጋለሁ በማለት ለፌዴራል ፖሊስ ፕሮፖዛሏን አስገባች።

ባቀረበችው ጥያቄ የተገረሙት የመርማሪዎች ቡድን እንሞክረው በሚል ሥራዋን እንድትጀምር አደረጉ።

ከዚያም ሰዎች በሚነግሯት ገለጻ ብቻ የወንጀለኞችን ፊት በመሳል ለፖሊስ ታስረክባለች።

ፖሊስም ይህንን ይዞ ወንጀለኞችን በማፈላለግ በተለያዩ ጊዜያት መረጃ አጥፍተዉ የተሰወሩ 1 300 ወንጀለኞችን መያዝ ችሏል።

ባልተለመደ መልኩ አይታቸው የማታውቃቸውን ወንጀለኞች በስዕል ጥበቧ አማካኝነት እንዲያዙ በማድረጓ የዓለማችን ስኬታማ የፎረንሲክ አርቲስት በሚል እየተሞካሸት ይገኛል።

በሂዩስተን ፖሊስ ዲፓርትመን ሥር የወንጀል ተጠርጣሪዎችን በመለየት የጊነስ ወርልድ ሪከርድ ይዛለች።

ጉዳቷን ወደ ድል በመቀየር ለበርካቶች እፎይታ ሆናለች ሲሉም በአሜሪካ የሚገኙ በርካታ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በአደጉት ሀገራት በደህንነት ካሜራ ወልም በፎቶ ምስላቸውን ማግኘት አስቸጋሪ የሆኑ ወንጀለኞችን ለመያዝ የሰዎችን ምስክርነት በመስማት ብቻ ሰዓሊዎች የተጠርጣሪዎችን መልክ እና አጠቃላይ ገጽታ ስለው ለፖሊሶች ያስረክባሉ።

 

 

በቢታኒያ ሲሳይ