Search

የመራጭነት ካርድዎ - የሀገርዎን ዕጣ ፈንታ የሚወስኑበት ቁልፍ

ሓሙስ መጋቢት 03, 2018 57

በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ ለመራጭነት መመዝገብ በሀገርዎ ጉዳይ ላይ የመወሰን ሥልጣን እንዳለዎት የሚያረጋግጡበት መብት ነው።
"ድምፄ ምን ያደርጋል?" ከሚል የተሳሳተ ስሜት ወጥቶ በሂደቱ ውስጥ አሻራን ለማሳረፍ የመጀመሪያው እና ወሳኙ እርምጃ ለመራጭነት መመዝገብ ነው።
ዜጎች አገር ወዳድነታቸውን በተግባር ከሚያሳዩባቸው መንገዶች በምርጫ ንቁ ተሳታፊ መሆን አንዱ ሲሆን፤ ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ ለሀገረ መንግሥት ግንባታና ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ምርጫ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
ለመራጭነት የተመዘገበ ዜጋ ነገ የሚመረጠውን አካል "ይህንን ቃል ገብተህ ነበር" ብሎ ለመጠየቅ መብት ይኖረዋል፤ የፖለቲካ ልዩነቶችን በጠመንጃ ሳይሆን በምርጫ ካርድ ለመፍታት መንገድ ይከፍታል፤ የፓርቲዎችን የፖሊሲ ልዩነት አይቶ ለራስና ለሀገር የሚበጀውን ሐሳብ ለመምረጥ ያስችላል።
የመራጭነት ካርድ መውሰድ የግል መብት ቢሆንም፣ ውጤቱ ግን ሀገራዊ ነው። ካርድ አለመውሰድ በአንጻሩ ሌሎች እንዲወስኑልዎ መፍቀድ ነው፤ የመወከል መብትንም ማጣት ያስከትላል።
ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ የመራጭነት ካርድዎን በመውሰድ የነገዋን ኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ዛሬ ይወስኑ!