Search

በጉዞ ላይ ያለችው የ113 ዓመቷ ኪሩና ቤተክርስቲያን

ረቡዕ ነሐሴ 14, 2017 146

113 ዓመቷ ኪሩና ቤተክርስቲያን በስዊድን ካሉት ሙሉ በሙሉ በእንጨት የተሰሩ ሕንፃዎች አንዷ ናት።

በድሮ ጊዜ  በአካባቢው ይካሄድ በነበረ የማዕድን ማውጣት ሥራ ምክንያት ኪሩና ቤተክርስቲያን የምትገኝበት አካባቢ መሬት የመሰንጠቅ አደጋ አጋጥሞታል ተብሏል። 

በመሆኑም ይቺን ታሪካዊ እና ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ከአደጋው ለመታደግ  ካለችበት ስፍራ በማንሳት ወደሌላ ቦታ በመጓጓዝ ላይ ትገኛለች

በከባድ የጭነት መኪና በሰዓት 500 ሜትር ፍጥነት  የምትጓዘው ቤተክርስቲያኗ ወደ ታሰበው አዲስ ስፍራ እስክትደርስ ሁለት ቀናት የሚወስድባት ሲሆን፤ ትናንትን ስትጓዝ በመዋሏ ዛሬ እንደምትድረስ ይጠበቃል 

የኪሩና ጥንታዊት ቤተክርስቲያን 35 ሜትር ከፍታ እና 40 ሜትር ስፋት ያላት ሲሆን፤ ክብደቷም 672 ቶን ገደማ ይደርሳል። 

ቤተክርስቲያኗ ከዚህ ቀደም የስዊዲን ውብ ኪነ ሕንጻ ተብላም ተመርጣለች።

እንዲህ ያለውን ታሪካዊ ሕንፃ ወደ ሌላ ስፍራ ማዘዛወር ታዲያ በጉዞ ወቅት የመፍረስ አደጋ ከፊቱ የተጋረጠበት በመሆኑ እምብዛም ያልተለመደ ነው። 

ሆኖም መሐንዲሶች ሕንፃውን ከማፍረስ ይልቅ በብረት ምሰሶዎች በመደገፍ እና በዝግታ የሚንቀሳቀሱ ማጓጓዣዎችን በመጠቀም እየገፉ መውሰድን መርጠዋል።

ከፈረንጆቹ 1950 በፊት የተገነባው የኪሩና ቤተክርስቲያን ግዙፍ ሕንጻፃን ጉዞ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች፣ ጎብኚዎች በመንገዱ ግራ እና ቀኝ በመሆን እየተመለከቱት ይገኛሉ።

በሴራን ታደሰ